• የየካቲት 15 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
    7 mins
  • የየካቲት 14 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    Feb 21 2025
    ከቀናት በፊት በሰሜን ጎጃም ዞን ጎንጂ ቆለላ ወረዳ በታጣቂዎች ታግተው የነበሩ 13 መምህራን ትናንት መለቀቃቸውን ቤተሰቦችና ጓደኞቻቸው ተናገሩ። ሌሎች ሁለት መምህራን መታገታቸው ተሰምቷል። ከመንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት ላደረጉ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት በምህጻሩ ኦነሰ አመራሮች በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሹመት ተሰጣቸው። በሱዳን እና በኬንያ መካከል የዲፕሎማሲ ግንኙነቱ ውጥረት ነግሶበታል። የሱዳን ወታደራዊ መንግሥት ትናንት በኬንያ የሚገኙ የሀገሪቱን አምባሳደር ጠርቷል። እስራኤል በሃማስ ታግታ ከነሕጻናት ልጆቿ የተገደለችው እናት አስከሬን እንዲሰጣት ጠየቀች።
    Show more Show less
    12 mins
  • የሐሙስ የካቲት 13 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    Feb 20 2025
    *ሰሞኑን ጋምቤላ ክልል፤ ኑዌር ዞን ውስጥ የተከሰተው በሽታ ኮሌራ መሆኑን የክልሉ ጤና ጽ/ቤት ዐሳወቀ ። እስከ ትናንት ምሽት ድረስ በጤና ባለሞያዎች የተረጋገጠ የኮሌራ በሽተኞች ቁጠር 192 መድረሱ ተገልጧል ። *ፈረንሣይ የመጨረሻ የጦር ሠፈሯን ለለኮት ዲቯር ዛሬ አስረከበች ። ይህም ፈረንሣይ ለዐሥርተ ዓመታት በምዕራብ አፍሪቃዊቷ አገር የነበራትን ወታደራዊ ይዞታ ሙሉ ለሙሉ እንዲያከትም የሚያደርግ ነው ተብሏል ። *ሐማስ በመስከረም 26ቱ ድንገተኛ ጥቃት እሥራኤል ውስጥ ካገታቸው 250 ሰዎች መካከል ሕይወታቸው ያለፉ ሦስት የቤተሰብ አባላትን እና የአንድ አዛውንትን አስክሬን ዛሬ አስረከበ ።
    Show more Show less
    9 mins
  • የዓለም ዜና
    11 mins
  • የየካቲት 11 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    Feb 18 2025
    -ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የተመሠረተበት 50ኛ ዓመት ለሁለት ከተከፈሉት የፓርቲዉ አንጃዎች በአንደኛዉ መቀሌ ዉስጥ ተከበረ።ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ በዓሉን ምክንያት በማድረግ መልዕክት አስተላልፈዋል።----የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር በሁለት የደቡባዊ ሱዳን መንደሮች በከፈተዉ ጥቃት በትንሹ 200 ሠላማዊ ሰዎች መግደሉን አንድ የመብት ተሟጋች ቡድን አስታወቀ።----የሩሲያና የዩናይትድ ስቴትስ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ሪያድ-ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ ባደረጉት ዉይይት የዩክሬኑ ጦርነት እንዲያበቃ የሚደራደር የባለሥልጣናት ቡድን ለመሰየምና የአሜሪካና የሩሲያ ግንኙነትን ለማሻሻል ተስማሙ።
    Show more Show less
    12 mins
  • የየካቲት 10 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    Feb 17 2025
    ጋምቤላ ክልል በ4 ወረዳዎች የተከሰተ «ኮሌራ መሰል» በሽታ የዘጠኝ ሰዎችን ሕይወት ቀጠፈ። በሶማሊያዋ ፑንትላንድ ከ240 በላይ እራሴን «እስላማዊ መንግሥት» የሚለው ታጣቂ ቡድን አባላት መገደላቸው ተገለጸ። የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ከፍተኛ ዲፕሎማትና የክሬምሊን አማካሪያቸውን ወደ ሳውድ አረቢያ ላኩ። የዩክሬንን ጦርነት ለማስቆም ለሚካሄደው ውይይት አዲሱ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሮቢዮ ሳውዲ ገብተዋል። የዩክሬን ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ኪየቭን ያላካተተ ውይይት ውጤት አይኖረውም አሉ። የእስራኤል ጦር ዛሬ ደቡባዊ ሊባኖስ ውስጥ ባካሄደው የአየር ድብደባ የሀማስን የጦር አዛዥ መግደሉን አስታወቀ።
    Show more Show less
    10 mins
  • የየካቲት 9 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
    8 mins
  • የየካቲት 08 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    Feb 15 2025
    የጅቡቲ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማሕሙድ አሊ ይሱፍ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሆነው ተመረጡ። ናይጄሪያዊው ባለጠጋ አሊኮ ዳንጎቴ የኦሞ ኩራዝ ስኳር ኩባንያን ለማስፋፋት ዕቅድ እንዳላቸው ተገለጸ። በኦሮሚያ ክልል ከመተሐራ ከተማ አቅራቢያ በሬክተር ስኬል 6.0 የተመዘገበ ርዕደ መሬት ተከሰተ። ሐማስ ሦስት ታጋቾች፤ እስራኤል 369 ፍልስጤማውያን እስረኞችን ዛሬ ቅዳሜ በቀይ መስቀል በኩል ተለዋወጡ። አሜሪካ ከዩክሬን ጀርባ ከሩሲያ ጋር ሥምምነት እንዳትፈጽም ፕሬዝደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ አስጠነቀቁ። መራኄ-መንግሥት ኦላፍ ሾልስ በጀርመን “ዴሞክራሲ ውስጥ የውጪ ጣልቃ ገብነትን” እንደማይቀበሉ ተናገሩ።
    Show more Show less
    9 mins