• የዓለም ዜና

  • By: DW
  • Podcast

የዓለም ዜና

By: DW
  • Summary

  • ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።
    2025 DW
    Show more Show less
Episodes
  • የየካቲት 15 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
    7 mins
  • የየካቲት 14 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    Feb 21 2025
    ከቀናት በፊት በሰሜን ጎጃም ዞን ጎንጂ ቆለላ ወረዳ በታጣቂዎች ታግተው የነበሩ 13 መምህራን ትናንት መለቀቃቸውን ቤተሰቦችና ጓደኞቻቸው ተናገሩ። ሌሎች ሁለት መምህራን መታገታቸው ተሰምቷል። ከመንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት ላደረጉ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት በምህጻሩ ኦነሰ አመራሮች በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሹመት ተሰጣቸው። በሱዳን እና በኬንያ መካከል የዲፕሎማሲ ግንኙነቱ ውጥረት ነግሶበታል። የሱዳን ወታደራዊ መንግሥት ትናንት በኬንያ የሚገኙ የሀገሪቱን አምባሳደር ጠርቷል። እስራኤል በሃማስ ታግታ ከነሕጻናት ልጆቿ የተገደለችው እናት አስከሬን እንዲሰጣት ጠየቀች።
    Show more Show less
    12 mins
  • የሐሙስ የካቲት 13 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    Feb 20 2025
    *ሰሞኑን ጋምቤላ ክልል፤ ኑዌር ዞን ውስጥ የተከሰተው በሽታ ኮሌራ መሆኑን የክልሉ ጤና ጽ/ቤት ዐሳወቀ ። እስከ ትናንት ምሽት ድረስ በጤና ባለሞያዎች የተረጋገጠ የኮሌራ በሽተኞች ቁጠር 192 መድረሱ ተገልጧል ። *ፈረንሣይ የመጨረሻ የጦር ሠፈሯን ለለኮት ዲቯር ዛሬ አስረከበች ። ይህም ፈረንሣይ ለዐሥርተ ዓመታት በምዕራብ አፍሪቃዊቷ አገር የነበራትን ወታደራዊ ይዞታ ሙሉ ለሙሉ እንዲያከትም የሚያደርግ ነው ተብሏል ። *ሐማስ በመስከረም 26ቱ ድንገተኛ ጥቃት እሥራኤል ውስጥ ካገታቸው 250 ሰዎች መካከል ሕይወታቸው ያለፉ ሦስት የቤተሰብ አባላትን እና የአንድ አዛውንትን አስክሬን ዛሬ አስረከበ ።
    Show more Show less
    9 mins

What listeners say about የዓለም ዜና

Average customer ratings

Reviews - Please select the tabs below to change the source of reviews.